Page 1
The Islamic Bulletin
Purpose Of Life In Amharic
የህይወት ትርጉሙ
ማንንም የመብላትን ጥቅም ብጠይቀው፣
“
ለምን እንመገባለን
?”
የአብዛኛው ሰውምላሽ የሚሆነው ተመሳሳይ አንድ ምላሽ
ነው፣
“
ለስነ
ምግብነቱ
”
ምክንያቱም ህይወትን የሚያስቀጥል ስለሆነ
::
ማንንም
ለምን ስራ እንደሚሰሩ ብጠይቃቸው፣ ምላሻቸው
የራሳቸውንና
የቤተሰቦቻቸውን ፍላጎት ለማሟላት
የሚል ይሆናል
::
ማንንም ለምን
እንደሚተኙ፣ ለምን እንደሚታጠቡ፣ ለምን እንደሚለብሱ
የመሳሰሉትን
ነገሮች ብጠይቅ ምላሻቸው
“
ለሁሉም የሰው ልጆች መሰረታዊ ፍላጎት
እንደሆነ ይነግሯችኋል
”
ይህን መሰል ብዙ መቶ ጥያቄዎችን ብንደጋግም
ምላሹ ተመሳሳይ ይሆናል፣ በማንኛውም ቋንቋ፣ በማንኛውም ቦታ፣
በቀላሉ ለመግለጽ በየትኛውም የአለም ክፍል ተመሳሳይ መልስ
::
ግን
ለምን
“
የህይወት አላማና ትርጉሙምንድን
ነው
?”
ብለን ስንጠይቅ
የተለያየ መልስ የምናገኘው
?
ምክንያቱም ሰው ግራ ተጋብቷልና
ነው፣
በትክክል ምን እንደሆነ አያውቁም
::
በጨለማውስጥ ይዳክራሉ
::
“
አላውቀውም
”
ላለማለትም እንዲህነው ተብለው የተሞሉትን፣ መልስ
ነው ብለው ይናገራሉ
::
ስለዚህ
ነገር ትንሽ እናስብ
::
የኛ የመኖራችን ትርጉም እንዲሁ
ለመብላት፣ ለመተኛት፣ ለመልበስ፣ ለመስራት፣ ሀብት ለማፍራት እና
ለመደሰት
ነው
?
በቃ ይህ
ነው የኛ የመኖራችን ትርጉም
?
ለምን ተወለድን
?
የመኖራችን ትርጉም ምንድን
ነው፣ አስገራሚ ከሆነውሁለንታ እና ከስነ
ፍጥረት በስተጀርባ ያለው ጥበብ ምንድን
ነው
?
ስለጥያቄው በደንብ
አስቡበት
!
አንዳንዶች ስለ ፈጣሪ ህልውና ምንም ማረጋገጫ የለም ብለው
ይከራከራሉ፣ ስለ አምላክ ማረጋገጫ የለም ይላሉ፣ ይህ ሁሉ ፍጥረት፣
ይህ ሁሉ ሁለንታ በፈጣሪ የተሰራ እንደሆነ ማረጋገጫ የለም ይላሉ
::
እንዲህም ብለው የሚያምኑ አሉ
:
አለሙሁሉ እንዲሁ በአጋጣሚ
የመጣ
ነው
::
በቢግ ባንግ መላው አለማት እንዲሁ ዝም ብሎ የመጣ
የተገኘ
ነው
::
ህይወትም ይህ
ነው የሚባል ሊገለጽ
የሚችል ትርጉም
የለውም በማለት ይከራከራሉ፣ ስለ አምላክ ስለ ህይወት ትርጉሙወይም
ስለ አለሙፈጣሪ ማረጋገጫ በሳይንስም ሆነ በ ሎጂክ ሊያረጋግጥ
የሚችል ምንም
ነገር
የለም
::
እዚጋ ከቅዱስ ቁርዐን ስለዚህ ጉዳይ የሚገልጹ
የተወሰኑ ቃላትን ልግለጽ
::
“
ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር ሌሊትና ቀንም በመተካካት ለባለ
አእምሮዎች በእርግጥ ምልክቶች አሉ
(
እነርሱም
)
እነዚያ ቆመው
ተቀምጠውም በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወድሱ
በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ ጌታችን ሆይ
!
ይህን
በከንቱ አልፈጠርከውም ጥራት ይገባህ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን
የሚሉ
ናቸው
::”
ቅዱስ ቁርዐን
3:190-191)
ከፊታችሁ ተገኝቼ ንግግር እንዳቀርብ እድሉ ስለተሰጠኝ ከፍ
ያለ ክብር ይሰማኛል
::
እናም ማለት
የምፈልገው ከፊታችሁ የቆምኩት
እንደ አዋቂ ለማስተማር አይደለም
::
እኔም እንደ አዋቂ ለማስተማር
ዝግጁ
ነኝ ብየ አላስብም
::
ከዛ ይልቅስ የራሴን ምክር ልመክር ብል
ይገልጸዋል
::
ምክንያቱም ራሴን ከፊቴ ካሉት ወንበሮች አስቀምጬ
አይዋለሁና
ነው
::
ከጥቂት ቀናት በፊት፣ ከጥቂት አመታት በፊት፣
ከጥቂት ጊዜያት በፊት
_
እኔም እናንተ ካላችሁበት ወንበር ላይ ተቀምጬ
ነበር፣ ከየትም ይምጣ
_
የመጣበት ትርጉም የለውም
::
ሰው ሆኖ ስለ
እስልምና ግንዛቤ የሌለው
::
እናም በዛች ቅጽበት፣ እኔም ያ ሰው
ነበርኩ
የህይወት ትርጉምን ምንም ያልተረዳና ያልገባው
!
ስለዚህ በዚህ አስታዋሽነት፣ እያልኳችሁ ያለሁት እንደ አዋቂ
ማስተማር ሳይሆን እንደ መረጃ እና እንደምክር እንድታስቡት
ነው
::
ላጋራችሁ ያሰብኩትም መረጃ ትንሽ ሰፋ ያለ ቢመስልም፣ የሰውን
የአዕምሮ ልቀት፣ የማቀናበር ችሎታውና የማከማቸት አቅሙን ስታስቡት
በእነዚህ ጥቂት
ገጽ መረጃወች በእርግጥም እንደማያጨናንቃችሁ
ልነግራችሁ እወዳለሁ
::
በዛሬው እለትም የምንወያይባቸውን
ነጥቦች ላሳውቃችሁ
ኃላፊነት አለብኝ
_
የህይወት ትርጉሙምንድን
ነው
?
እናም ደግሞ
የሚከተሉትን ይጠይቃል
_ “
ስለ እስልምና ምን ታውቃላችሁ
”
ማለት
_
ስለ እውነት ስለ እስልምና ምን ታውቃላችሁ
?
ስለ እስልምና
የሰማችሁትን አይደለም፤ ወይም ደግሞ አንዳንድሙስሊሞች
ስለሚያደርጉት አይደለም፣ ግን ስለ እስልምና ምን እንደምታውቁ እንጂ
?
ይህን እድል ስላገኘሁ ክብር ይሰማኛል፣ ሁላችሁም እኩል
ኃላፊነት አለባችሁ ብየ ብጀምር ደስ ይለኛል
::
እና ያ ኃላፊነት ማንበብ
ወይም ማደመጥ
ነው
_
በንጹህ ልቦና እና በሚያገናዝብ አዕምሮ
::
ባለማወቅ እና በባህል ተጽዕኖ በተሞላች አለምውስጥ
ከድርጊታቸው በፊት ላማሰብ ትንሽ ጊዜ
የሚሰጡ ሰወችን ማግኘት
ይበልጥ አስቸጋሪ ሆኗል
::
ስለ ህይወት እውነታ ለማሰብ፣ የዚህችን አለም
እውነት ለመድረስና የነፍሳችንን ዋጋ ለማወቅ፣ እንዳለመታደል ሆኖ ግን
አብዛኛውን ሰው እጅግ መሰረታዊና ጠቃሚ የሆነውን ጥያቄ
“
የህይወት
ትርጉሙምንድን
ነው
”
ብላችሁ ስትጠይቁት በማየት እና
ነገሮችን
በመገምገም ምላሽ መስጠት
የማይችሉ ናቸው
::
በብዙ አጋጣሚዎችም፣
ሌላ የሆነ ሰው ሲል
የሰሙትን ሊነግሯችሁ ይችላሉ ወይም የወል የጋራ
የሆነ አስተሳሰብ ሲያንጸባርቁ ይስተዋላሉ
::
አባቴ ስለህይወት ትርጉም እንደተናገረው፣
የቤተክርስቲያኒቱ ሚኒስቴር
እንደተናገረው፣
የትምህርት ቤቴ መምህር እንደተናገረው፣ ጓደኛየ
እንደተናገረው
::