አስደናቂው የእስልምና ጉዞየ

በቅርቡ አንዱ እንዴት ወደ እስልምና ህይወት እንደመጣሁ ሲጠይቀኝ፣ በአግራሞት ወደኋላ ተመለስኩ:: ወደ እስልምና ህይወት መምጣቴም የህይወቴ ወሳኝ ነጥብ ይሆናል ብየ ፈጽሜ አስቤ አላውቅም:: መቼ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ካቶሊክነትን የጠየኩኝ? መቼ ነበር ሙስሊም ለመሆን የፈለኩኝ? ለእነዚህ ጥያቄወችና መሰሎቹ መልስ ለመስጠት ከማስበው በላይ ይበልጥ ማገናዘብ ይጠይቃል:: የእውነት ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠትም እስልምና እንድቀበል እና እውነታውን እንዳውቅ የመራኝን ነገር እንድትረዱት ከስር መሰረቱ ከመጀመሪያ መጀመር ያስፈልገኛል:: ሙስሊም የሆንኩት በ 67 አመቴ ነው፣ እናም አምላክን በእስልምና አማኝ እንድሆን ስለባረከኝ አመሰግነዋለሁ::

“አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለእስላም ይከፍትለታል ሊያመመውም የሚሻውን ሰውደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት እንደሚታገል ያደርገዋል:: እንደዚሁ አላህ በነዚያ በማያምኑት ላይ ርክሰትን ያደርጋል”

(ቅዱስ ቁርዐን 6: 125)

እኔ ያደግሁት በአጥባቂ ሮማን ካቶሊክ ቤት ነው፣ ከሶስት ሴቶች ልጆች መካከለኛዋ ነኝ:: አባቴ በየቀኑ ለረጅም ሰዐት በታታሪነት ይሰራል:: በጠዋቱ ወደ ስራ ይሄዳል አምሽቶም ይመለሳል:: ይህን ሁሉ የሚያደርገው እናቴ ቤት በመዋል እህቶቼንና እኔን እንድትንከባከብ ነው:: ከእለታት በአንድ እድለ ቢስ ቀን እናታችን የሚያስከፋ ነገር ነገረችን ይሀውም አባታችን የመኪና አደጋ እንደደረሰበት ነበር:: ህይወቱም እንዲሁ በድንገት አለፈ የቤተሰቡም ህይወት ተመሰቃቀለ:: በዚህ ሁሉ የለውጥ ክስተት፣ እናታችን ወደ ስራ መግባት እንዳለባት ነገረችን:: እናቴ፣ ነርስ የነበረች ሲሆን፣ አሁን እኛን ለማስተዳደር ለመስራት ተገደደች:: በአቅራቢያ በሚገኝ ሆስፒታልም ስራ አገኘች፣ በብዛት በሁለት ፈረቃ ትሰራለች:: ግን በተከሰተው ለውጥ ምክንያት ባላት ኋላፊነት፣ እናታችን የኛን አስተዳደግ በአግባቡ መቆጣጠር አልቻለችም:: እና ቢሆንም ወደ ካቶሊክ ትምህርት ቤት ላከችን፣ ስራዋም በሴት ልጆቿ ላይ ቁጥጥር ማድረግ አላስቻላትም::

ስለዚህም፣ ብዙ የማሳልፋቸው ጊዜወች ነበሩ፣ እኔም ከጓደኞቼ ጋር በአቅራቢያ ባሉ ካፌወች መዝናናት ጀመርኩ:: እዛ ነበር የወደፊት ባሌን ያንን ትሁት ሙስሊም ሰው ያገኘሁት:: እናቴም ጊዜየን ከዚህ ሰው ጋር እንደማሳልፍ አታውቅም ነበር:: በርግጥ፣ ከዚህ ሰው ጋር እንደተፋቀርኩ እና ማግባት እንደምፈልግ ስነግራት፣ ከተለያየ ማንነት የመጣንና ኋላ ላይ ችግሮች እንደሚፈጠሩብን ያስጠነቀቀችኝ:: በወደፊታችንም ልጆች ካሉ ያለምንም ጥርጥር በሀይማኖት ምክንያት ችግሮች እንደሚፈጠሩ ደመደመች:: በሀያ አመት እድሜዬ፣ በጋብቻችን ላይ ችግር ይፈጠራል ብየ አላሰብኩም:: ያ ሰው እኔን ስለሚንከባከበኝ በጣም ደስተኛ እና በፍቅር ውስጥ ነበርኩ:: በዚያን ጊዜም ባለቤቴ ያን ያህል አጥባቂ ሀይማኖተኛ ስላልነበር፣ ወደ ካቶሊክ እምነት ልቀይረው እንደምችል ይሰማኝ ነበር:: ተመሳሳይ ብሄርና ማንነት ስላልነበረን ፣ እራሴን ይበልጥ ግልጽ እና አዲስ ባህሎችን ለመቀበል ዝግጁ የሆንሁ እንደሆንኩ ይሰማኛል::

ለቀጣዮች ብዙ አመታትም ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ የሚጓዝ ይመስል ነበር:: ደስተኞችም ነበርን ባህል ወይም ሀይማኖት ለአንድ ጊዜ እንኳ ችግር አልፈጠሩብንም:: አምላክም በመልከ መልካም ወንድ ልጅ ባረከን ከብዙ ቀጣይ አመታት በኋላም በቆንጆ ሴት ልጅ ተባረክን:: አሁንም፣ በህይወት መስመራችን እንደቀጠልን ነው እንደውም ልጆቼን ወደ ቤተ ክርስቲያን ከእኔ ጋር መውሰድ ጀመርኩ:: ባለቤቴ የሰንበትን ሳምንታዊ ጉባኤ እንዳልሳተፍ በፍጹም ከልክሎኝ አያውቅም:: ልጆቻችንን ቤተ ክርስቲያን መውሰድ ከጀመርኩ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ፣ ያኔ ነበር ልጆች ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ አለመፈለጉን በግልጽ የተናገረው:: ግልጹን ለመናገር፣ በጣም ተናድጄ እና ተበሳጭቼ ነበር:: “ግን ለምን አይሆንም፣” ጠየቅሁ:: “የትኛውም ሀይማኖት ከየትኛውም አይሻልም፣” ተከራከርኩ:: እነሱን ወደ ቤተ ክርስቲያን መውሰዱ ጉዳቱን ልገነዘበው አልቻልኩም:: እስከዚህ ደረጃ ድረስ፣ ስለ ሀይማኖት በፍጹም ተወያይተን አናውቅም:: በርግጥ፣ ከካቶሊክነት የተለየ ሀይማኖት ይኖራል ብየ በፍጹም ጠይቄ እንኳን አላውቅም:: የተወለድኩት ከካቶሊክ ስለነበር ካቶሊክነት ትክክለኛው ሀይማኖት ነው ብየ አስብ ነበር:: ለማብራራት ያህል ጣቴን እንኳ መቀሰር የማልችል፣ ከዚህ ቀን ጀምሮ፣ ብዙ ችግሮች እየተገለጡ መጡ:: ሁልጊዜ እንከራከራለን _ ስለ ሁሉም ነገር እና ስለ ሁሉም ሰው:: አሁን ላይ፣ ትንሿ ነገር ትልቅ ጉዳይ መሆን ጀመረች:: ሀይማኖት በመሀከላችን የመከራከሪያ ነጥብ ሆነ:: የባህል ልዩነታችን የመከራከሪያ ነገር ሆነ:: ስለ አማቶቻችንም እንከራከራለን እናም በጣም እንዳለመታደል፣ በልጆቻችን አስተዳደግ ላይ እንከራከራለን:: እናቴ አስጠንቅቃኝ የነበረው ነገር ሁሉ እውነት እየሆነ መጣ::

ብቸኛው በሁለታችን መሀል ያለ ሰላማችን እና የሚያስማማን የባለቤቴ አባት አማቴ ለትዳራችን ያለው ብልህነት፣ ቅንነት፣ መጨነቅ እና ፍቅር ነው:: አማቴ ልጁንና የልጅ ልጆቹን የሚወድ፣ እንዲሁ ደግሞ እኔንም በሚከበር መልኩ እንደልጅ የሚወደኝ ነው:: እርሱም በጣም ሀይማኖተኛ እና አጥባቂ ሙስሊምና ብልህ ሰው ነበር:: በዚያን ጊዜ፣ ከእስላም ባለመቀራረቤ ምክንያት፣ አማቴ ስለ እስላም እንደ መግቢያ የሆኑኝ የመጀመሪያው ሰው ናቸው:: እያንዳንዷን የጸሎት ሰዐት ይጸልያል፣ በረመዳን ወር ይጾማል፣ እንዲሁም ለድሆች በጣም ቸር ነው:: ከፈጣሪ ጋር ያለው ግንኙነት ይሰማኛል:: በርግጥም፣ አማቴ በጣም ደግ የነበረና በየእለቱ ከመስጊድ የከሰዐት ጸሎት በኋላ ችግረኛ ሰወችን ምሳ አብረውት እንዲመገቡ ይጋብዝ የነበረ ነው:: ይህ የየዕለት ተግባሩ ነበር:: እስከ 95 አመቱ እለተ ሞቱ ድረስ በዚህ ተግባር እንደቀጠለ በቅርብ የሚያውቁት ያስታውሳሉ::

አማቴም በባለቤቴና በእኔ መካከል ባለው አለመግባባት ምክንያት ልጆቻችን በጠባችን ምክንያት ከመጎዳታቸው በፊት መፍትሄ እንድንፈልግለት አማከሩን:: እስከመጨረሻው ድረስም መፍትሄ እንድናገኝለት ሞከረ:: ልጁንም የራሴን ሀይማኖት እንዳካሂድ ቦታ መስጠት እንዳለበት አስጠነቀቀው፣ ግን እዚህ ላይ ስለ ሀይማኖት ብቻ አልነበረም:: ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ውስጥ ስለነበርኩ ማረፍ ፈለኩ:: ባለቤቴንም እንድንለያይ ስጠይቀው፣ ተስማማ ይህም ለትዳራችን የተሻለው ነገር ነበር:: አባባሉ እንደሚለው “መለያየት ልብ ይበልጥ እንዲያፈቅር ያደርጋል::” በኛ ላይ ግን ይህ አልሆነም:: እንደውም መለያየታችን ልባችን ይበልጥ እንዲቆራረጥ አደረገው እንጂ:: ከመለያየታችን በኋላም፣ ሁለታችንም ቋሚ መለያየትን በመምረጥ በፍቺ ተስማማን:: ልጆቼ ከእኔ ጋር እንዲኖሩ ብፈልግም፣ ሁለታችንም በአባታቸው ቢያድጉ ይበልጥ ለልጆቹ የተሻለ እንደሆነ ስለተረዳን በዚሁ ተስማማን:: እሱ በገንዘብ ደረጃ በጣም የተሻለ የነበረና፣ እነሱን ለማሳደግ እና እኔ ለመስጠት ያልተዘጋጀሁበትን ምቾት ይሰጣቸው ዘንድ የተስማማ ነበር:: ሁሌም ምሽት እንዴት እንደምናፍቃቸው:: ከእናቴ ጋር በመሆን ልጆቼን በየሳምንቱ እጎበኛቸው ነበር:: የቀድሞ ባለቤቴም ልጆቻችንን አርብ ከሰዐት እኔ ጋር ካመጣቸው በኋላ እሁድ ጠዋት መልሶ ይወስዳቸዋል:: ምንም እንኳ ይህ ነገር ስሜት የሚጎዳ ቢሆንም፣ ከምንም ይሻላል::

በእያንዳንዱ ምሽት ወደ መኝታየ ከመሄዴ በፊት፣ መጽሀፍ ቅዱስ አነባለሁ:: ልጆቼ በሚጎበኙኝ ሰዐትም፣ ልጆቼ ይረዱትም አይረዱትም አንድ አርዕስት አነብላቸዋለሁ:: ለልጆቼ ካነበብኩላቸው በኋላ፣ አንድ ምሽት ከእየሱስ እርዳታ ፈለኩ፣ ቀጣይ ምሽት ከመላዕክት፣ ቀጣይ ምሽት ከተለያዩ ቅዱሳን፣ ቀጣይ ምሽት ከድንግል ማርያም:: ግን አንድ ቀን የምንጠይቀው አንድስ እንኳ አልነበረንም፣ ቅዱሳኖች አለቁብኝ:: ስለዚህም “አሁን አምላክን መጠየቅ አለብኝ” አልኩ:: ልጄም “እሽ፣ አምላክ ማነው?” አለኝ፣ እኔም “እርሱ አንተን የፈጠረ፣ እኔን የፈጠረ ነው” አልኩት:: ምንጊዜም ቢሆን ከጎናችን ነው:: እናም እያሰላሰለ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ያስብ ነበር:: ለማብራሪያየም፣ በድጋሚ መስቀሌን አሻሸሁ:: አምላክንም አመሰገንሁት:: መስቀሌንም እየተመለከት እንዲህ አለኝ “እናቴ ይህ ማነው?” እኔም “ይህ አምላክ ነው:: የአምላክ ልጅ ነው” አልኩት ልጄም እንዲህ አለኝ “ከደቂቃወች በፊት አምላክ ዘላለማዊ ነው ብለሽኝ ነበር:: ይህ ከሆነ እንዴት ሞተ?” ብሎ ጠየቀኝ:: እኔም በህይወቴ ፍጹም፣ ፈጽሜ አስቤው የማላውቀው እውነታ ነበር:: እንዲህ ብሎም ጠየቀኝ ይህ አምላክ ከየት ተገኘ? እኔም በምላሹ እንዲህ አልኩት፣ የመጣ የተገኘው ከማርያም ማህጸን ፣ ከድንግል ማርያም ነው አልኩት:: እርሱም በመገረም “እህ….. ስለዚህ ከሆነ ጊዜ በፊት የተወለደ ነበር አለኝ;: እኔም በሚገባ አወ አልኩት:: ግን በመቀጠል እንዲህ አለኝ “አንቺ ግን ዘላለማዊ እንደሆነ ነግረሽኛል:: የማይሞት የማይወለድ እንደሆነ ተናግረሻል አለኝ:: ልጄ የስምንት አመት ልጅ ሲሆን፣ በቀጥታ እንዲህ ብሎ ጠየቀኝ፣ “እናቴ፣ ለምን ከአምላክ በቀጥታ እርዳታ አትጠይቂም” አለኝ እኔም ልጄ ሀይማኖቴን ጥያቄ ውስጥ በመክተቱ በአግራሞት በመደነቅና በሚነዝር ስሜት ውስጥ እንደነበርኩ ትዝ ይለኛል:: እኔም አምላክንም ደግሞ እንደምጠይቅ ነገርኩት:: ይህ የኔ ልጅም የኔ የማይናወጽ ዙፋን አቅኚ እንደሆነ በሚገባ አልተረዳሁም ነበር፣ ሁሌም የሚያስታውሰኝ እውነተኛውንና አንዱን አምላክ እንዳመልክ ነበር:: ምስጋና ይሁን ለአምላክ::

እኔም ከጥቂት አመታት በኋላ በድጋሚ በማግባት ከአዲሱ ባለቤቴ ጋር ወደ አውስትራሊያ ተዛወርኩ:: የቀድሞ ባለቤቴም ቤተሰቦቹን ይዞ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተንቀሳቀሰ:: ልጆቼን ለማየት በጉጉት ብጠብቅም ግን ጣልያን ውስጥ አዲስ ቤተሰብ መስርቼ የሶስት ተጨማሪ ሴት ልጆች እናት እስክሆን ድረስ አልተሳካም ነበር:: እስከዛም፣ የእያንዳንዷ ምሽት ጸሎቴም፣ “ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ” ስም ነበር:: አመታት በውጥረት እና በፍጥነት ነበር ያለፉት:: አንደኛው ክረምትም የሚያስደስት ነበር፤ እርሱም ወንዱ ልጄና ሴቷ ልጄ ሊጎበኙኝ መምጣታቸው ነው:: በጣም ብዙ ነገሮችም በአዕምሮየ ውስጥ ተሯሯጡ:: ከረዥም ጊዜ መለያየት በኋላ እኔን በማየታቸው ይደሰቱ ይሆን? ስለምንስ እናወራለን? ለእርዳታ ጸለይኩ:: ለመጀመሪያ ጊዜ ፍራቻየ ሁሉ ተኖ የጠፋው አየር ማረፊያ ውስጥ ልጆቼን በአይኔ እንዳየሁ ነበር:: ትንሽ ጊዜም ትለፍ በእናትና በልጅ መካከል ያለ ተፈጥሯዊ የሆነ የሚያስተሳስር ነገር አለ:: ወንዱ ልጄም ከሴቷ ይልቅ ተግባቢ ነበር:: የአሳማ ስጋ እንደማይመገቡ፣ በውስጣቸው አልኮል ያለባቸውን ምግቦችም እንደማይመገቡ ለማረጋገጥ አስታወሰኝ:: እኔም ስለ ሀይማኖቱ እንደማስታውስ ነገርኩት:: እንዲሁም ደግሞ የአሳማ ስጋ እንደማልመገብና አልኮልም እንደማልጠጣ ነገርኩት፣ ይህ ልምዴ የመጣው ከአባቱ ጋር ከተጋባን ጊዜ ጀምሮ ነበር:: በወይን በኩል ግን፣ እነርሱ እኔ ቤት እስካሉ ድረስ ምግብ ለማብሰል እንደማልጠቀምበት አረጋገጥኩላቸው::

በጣም ማራኪ ክረምት ነበር ያሳለፍነው፣ እርስ በእርስ ተዋውቀናል የእነርሱን አዲስ እህቶች አውቀዋል፣ አብረን በልተናል፣ ተዝናንተናል፣ ዋኝተናል ፤ እንዲያበቃም አልፈለኩም ነበር:: ግን የእነርሱ ህይወት ሳዑዲ አረቢያ ስለሆነ መመለስ እንደሚፈልጉ አውቃለሁ:: ሴቷን ልጄንም ድፍረት የመላበት ጥያቄ ጠየኳት ይሀውም ከእንጀራ እናቷ ጋር ግንኙነቷ ምን እንደሚመስል ነበር ፤ እርሷም ልክ እንደ ልጅ እንደምታያት ስትነግረኝ የእውነት ነበር ደስታ የተሰማኝ::

ልጆቼም ከዛ ክረምት በኋላ አንድ ላይ በመሆን ለተጨማሪ ሁለት ጊዜ ጎብኝተውኛል:: ወንዱ ልጄም 21 አመት ሲሆነው ለስድስት ወራት አብሮኝ ለመኖር መጣ:: ስለ ሀይማኖትም መከራከር እንችላለን_ ከልጄ ጋር ስለ ሀይማኖት መከራከር እንችላለን:: ወንዱ ልጄ እና እኔ የሚመሳሰል የግል ባህርይ ቢኖረንም፣ የራሳችን የሆነ ልዩነት ግን አለን፣ በጣም ግልጽ የሆነው ልዩነታችንም፣ እኔ ባለመግባባት ጊዜ ግልፍተኛ ስሆን፣ ልጄ ግን የተረጋጋ ነው፣ ስለዚህ እኔ በግልፍተኝነት የእብደት ድንበር ላይ ብሆን እንኳ የእርሱ የተረጋጋ ባህርይው አይለወጥም! ከዚህ ግጭት በስተቀርም፣ በውይይታችን መሀል የሚያግባባን ነገር ላይ እንደምንደርስ አምናለሁ:: እኛ ሁለታችንም መውደዳችን፣ ደግነታችንና የምንረዳ መሆናችን ይበልጥ ያመሳስለናል:: ከሁሉም ይበልጥ ስለ ልጄ የማደንቀው ነገር ደግሞ ለሚያደርገው ነገር ያለው ትኩረት ነው:: በጣም ተወዳጅ፣ ትሁት ሲሆን፣ግን ያለመውንና በአዕምሮው የያዘውን ለማሳካት ጠንካራ ስነ ምግባር ያለው መሆኑን በጣም አከብርለታለሁ:: በጣም በሚያስጨንቁ ሁኔታወች ውስጥ እንኳ ያለው ስዕብናውን የመጠበቅ ችሎታውን የማደንቅለት ነው:: በጣም ተገቢ አስተሳሰብ ያለውና በችግሮች ላይ የማያጣውር ነው:: በተቻለው መጠን ለችግሮች መፍትሄ የሚፈልግ እና ለማግለል የሚሞክር ነው:: የልጄ ልቦናም ወደ ካቶሊክነት እንዲቀየር ይመራው ዘንድ መጸለዬን ቀጠልኩ፣ እጅግም አድርጌ ልጄ ቄስ ይሆን ዘንድ ተመኘሁ፣ ርትዕ ሰባኪ እንደሚሆንም ታውቆኛል:: እሱም ጥሩ እና አምላክን የሚፈራ ልጅ ነው:: ለቄስነትም ጥሩ መስፈርት የሚያሟላ:: እናም አንዴ እርሱ ደንበኛ ቄስ እንደሚወጣው ስነግረው፣ ልጄ ፈገግ ብሎ እርሱ የካቶሊክ ቄስ ከሚሆን ይልቅ፣ እናቱ ሙስሊም ብትሆን እንደሚቀል ነገረኝ::

ከስድስት ወር በኋላም፣ ልጄ ወደ አሜሪካ መሄድ እንደሚፈልግ ገለጸልኝ:: ወደ አሜሪካ በመዛወርም መኖሪያውን በማያሚ፣ ፍሎሪዳ አደረገ:: ይህ ሆኖ ሳለ፣ እኔ ከቤት ከቀረችዋ ኮረዳ ልጄ ጋር ጋለሞታ ሆኜ መኖር ጀመርኩ:: ወንዱ ልጄም አሜሪካ ከእርሱ ጋር እንድኖር ይወተውተኝ ጀመር፣ ስለዚህም ከ 17 አመት ልጄ ጋር በመሆን ወደ ስቴትስ ሄድኩ:: አሜሪካንም ይበልጥ ወደድነው፣ ሴቷ ልጄም በፍጥነት ራሷን ከአካባቢው ጋር አላመደች:: የልጄ አቋምም ምንም አልተለወጠም እናም እኔ_እኛ ስለ ካቶሊክና እስላም ማውራት ብንቀጥልም ማንኛችንም አልተረታታንም:: አንዳንድ ጊዜ የስላሴ ጉዳይ ሲነሳና ምንም አይነት ምላሽ ሳጣ ወይም አጸፋ መመለስ ሲያቅተኝ፣ እጄን አንስቼ ትቼ እሄዳለሁ:: እሱ የእኔን

“ለምን እንደ ሁሉም መሆን አትችልም”፤ “ሌሎች ሙስሊሞች ይቀበሉኛል ሊሰብኩኝም አይሞክሩም” ብየ ስጠይቀው፣ “እኔ እንደ ሁሉም አይደለሁም” በማለት መለሰልኝ:: “እወድሻለሁ፣ ልጅሽ እንደመሆኔ ላንቺ ገነት ትገቢ ዘንድ እፈልጋለሁ” አለኝ:: እኔም ጥሩ፣ ታማኝ ሴት፣ የማልዋሽ፣ የማልሰርቅና የማላጭበረብር ሴት ስለሆንኩ ገነት እንደምገባ ነገርኩት:: ልጄም መልሶ እንዲህ አለኝ፣ “እነዚህ ነገሮች በዚህ አለማዊ ህይወት አስፈላጊና ጥሩ ናቸው፣ ይሁን እንጂ ቅዱስ ቁርዐን ደጋግሞ እንዳስቀመጠው አላህ ሸሪኮችን(ከአንድ በላይ አምላክ የሚያመልኩትን) ይቅር አይልም:: ቅዱስ ቁርዐን እንደሚያትተውም አምላክ ይቅር የማይለው ብቸኛው ሀጢያት ከእርሱ ጋር ቤተሰብ የሚያያይዙትን እንደሆነ ተናግሯል፣ ግን እርሱ የፈቀደውን የትኛውንም ቢሆን ይቅር ይላል:: ልጄም እንዳነብ እስልምናን እንዳውቅና እንድማር ለመነኝ:: መጽሀፍ ከመጣ ምናልባትም ልቦናየን ልከፍት እችላለሁ:: እምቢ አልኩ:: በካቶሊክነት ተወልጃለሁ በካቶሊክነት እሞታለሁ::

ለቀጣይ 10 አመታት፣ ከልጄ፣ ከባለቤቱና ከቤተሰቡ ጋር መኖር ቀጠልኩ:: እንዲሁ ደግሞ ሳዑዲ አረቢያ ከምትኖረው ልጄ ጋር የተወሰነ ጊዜ አብሪያት ማሳለፍ ፈለኩ:: ወደዛ ለመሄድ በቀላሉ ቪዛ አይገኝም ነበር:: ልጄም እስልምናን ብቀበል፣ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት ቪዛ ይሆነኝ እንደነበር፣ የዑምራ(ወደ መካ ሀጂ ማድረግ፣ ለሳዑዲ አረቢያ ቪዛ) ቪዛ ማግኘት እንደምችል በቀልድ ነገረኝ:: እኔም በሀይለ ቃል ሙስሊም እንዳይደለሁ ነገርኩት:: ከረዥም ልፋትና ከጥቂት ግንኙነቶች በኋላ፣ የሶስት ልጆች እናት የሆነችውን ልጄን እጎበኛት ዘንድ የጎብኝ ቪዛ ተሰጠኝ:: ከመሄዴም በፊት፣ ልጄ በሰቀቀን እቅፍ አድርጎ ይዞኝ፣ ምን ያህል እንደሚወደኝና ምን ያህል ገነትን እንደሚመኝልኝ ነገረኝ:: በመቀጠልም እንዲህ አለኝ፣ ከእናቱ ሙስሊም ያለመሆን በስተቀር በህይወቱ የፈለገውን ነገር ሁሉ እንዳገኘ ነገረኝ:: እርሱም ዕለት በዕለት ለአምላክ ልቦናየን እንዲቀይረው እንደሚጸልይ ነገረኝ:: እኔም ያ መቼም እንደማይሆን ነገርኩት::

ልጄን ሳዑዲ አረቢያ ሄጄ ጎበኘኋት:: ከሀገሪቱ፣ ከአየር ንብረቱ፣ ከህዝቡ ጋር በፍቅር ወደቅሁ:: በ 6 ወራት ውስጥ መመለስ ስላልፈለኩም እንዲራዘምልኝ ጠየቅሁ:: በቀን ውስጥም አዛን(የጸሎት ጥሪ) ለ 5 ያህል ጊዜ እሰማለሁ፣ ምዕመናንም ሱቆቻቸውን በመዝጋት ወደ ጸሎት ይጓዛሉ:: ምንም እንኳ ይህ ልብ የሚነካ ቢሆንም፣ መጽሀፍ ቅዱስ ጠዋትም ሆነ ማታ ማንበቤንና ጸሎት ማድረሴን ቀጥየበታለሁ:: ለአንዴ እንኳን ሴት ልጄም ሆነች ሌሎች ሙስሊሞች ስለ እስልምና ወይም እንድቀየር ሊሰብኩኝ አልሞከሩም:: እኔን በማክበር ሀይማኖቴን እንድተገብር ፈቅደውልኛል::

ልጄም እኔን ለመጎብኘት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊመጣ ነው:: በጣምም ደስ ብሎኝ ነበር _ በጣም ናፍቄውም ነበር:: ምንም ቆይቶ ቢመጣም እኔን አልተወኝም፣ ስለ ሀይማኖትና ስለ አምላክ አንድ መሆን ያወራልኛል:: እኔም ተናደድኩኝ:: እኔ ሳዑዲ አረቢያ ለአንድ አመት ያህል ስኖር አንድስ እንኳ ስለሀይማኖት የተናገረኝ እንዳልነበር ነገርኩት:: እናም እርሱ፣ ገና በሁለተኛው ምሽት ስብከቱን ለመጀመር ፈጠነ:: ይቅርታ በመጠየቅም በድጋሚ እስልምናን እንድቀበል ምን ያህል እንደሚፈልግ ነገረኝ:: እኔም ክርስትናየን በፍጹም እንደማልቀይር ደግሜ ነገርኩት:: ስለ ስላሴወችም በመጠየቅ እንዴት በአንድ ስሜት በማይሰጥ ነገር ላምን እንደቻልኩ ጠየቀኝ:: እኔም ሁሉም ነገር ስሜት መስጠት ሊገባው እንደሌለበትና እምነት ሊኖር እንደሚገባ ነገርኩት:: እርሱም ይህንን አባባሌን የተቀበለ መመምሰሉ በሀይማኖት ዙሪያ ያደረግነውን ውይይት በማሸነፌ በጣም ተደሰትኩ:: በመቀጠልም የእየሱስን ተዐምር እንዳብራራለት ጠየቀኝ:: ወደ ሆነ አቅጣጫ እየመራሁት እንዳለሁም ተሰማኝ:: እኔም የእየሱስን ተዐምራዊ ውልደት፣ ስለ ድንግል ማርያም፣ እየሱስ ስለ ሀጢያታችን መሞቱ፣ አምላክ ቅዱስ መንፈሱን በእርሱ ላይ መተንፈሱን፣ እየሱስ እንደ አምላክ፣ እየሱስ እንደ አምላክ ልጅ የሚለውን ሁሉ አብራራሁለት:: በምናገርበት ጊዜ ሁሉ በጥሞና ያደምጠኝ ነበር_ልጄ ያለምንም ማደናቀፍ በጸጥታ ያደምጠኛል:: በመቀጠልም በጥሞና አንድ ጥያቄ ጠየቀኝ፣ “እናቴ፣ እየሱስ ስለ ሀጢያታችን በዕለተ አርብ ከሞተ፣ አንች እንደተናገርሽው ከብሄረ ሙታን የተነሳው ከ 3 ቀን በኋላ በዕለተ እሁድ ነው፣ እንዲህ ከሆነ እነዚያን 3 ቀናት አለሙን ማን አስተዳደረ? እናቴ፣ ይህን አብራሪልኝ!” ብሎ ጠየቀኝ:: በዚያን ሰዐት ለጥያቄው ስነአመንክድ ለማሰብ ብሞክርም፣ ስሜት እንደማይሰጥ አወቅሁኝ::

እንዲህም አልኩ “እየሱስ የአምላክ ልጅ ነው:: እየሱስ እና አምላክ አንድ እና እኩል ናቸው::” አልኩት:: ልጄም መልሶ “ላሞች ጥጃ አሏቸው፤ ትንሽ ላሞች:: ድመቶች ግልገል አሏቸው፤ ትንንሽ ድመቶች:: ሰወች ልጆች አሏቸው፤ ትንንሽ ሰወች:: እንዲህ ሆኖ ሳላ አምላክ ልጅ ሲኖረው፣ እርሱ ምን ይሆናል? ትንሽ አምላክ? እንዲያስ ከሆነ፣ ሁለት አምላክ አለሽ? ቀጥሎም ጠየቀ፤ “እናቴ፣ አንቺ አምላክ መሆን ትችያለሽ?” ሲለኝ፣ ምን አይነት የማይረባ ጥያቄ እንደሆነ ነገርኩት:: ሰወች አምላክ መሆን አይችሉም:: (ይሄኔ በጣም ተበሳጭቼ ነበር) ቀጥሎም ጠየቀኝ፣ “እየሱስ ሰው ነበር?” ሲለኝ “አወ” አልኩት:: በመቀጠልም “ስለዚህ፣ እርሱ አምላክ ሊሆን አይችልም” አለኝ:: በርግጥ አምላክ ሰው ሆነ የሚለው ማረጋገጫ በራሱ የማይመስል ነው:: አምላክ በሰው ልጅ ባህሪ መለካቱም የማይመጥነው ነው ምክንያቱም ፈጣሪ ፍጥረቱን ሆነ እንደማለት ነው:: ምንም እንኳ፣ ፍጥረት የፈጣሪ የፈጠራ ውጤት ነው:: ፈጣሪ ፍጥረቱን ከሆነ፣ ፈጣሪ ራሱን ፈጠረ እንደማለት ነው ይህም ምንም የማይመስል ዘበት ነው:: ለመፈጠር፣ ከመጀመሪያው አለመኖር ያስፈልጋል፣ እናም ካልነበር እንዴት ሊፈጥር ይችላል? ከዚህ በተጨማሪም፣ ከተፈጠረ፣ መነሻ አለው ማለት ነው፣ ይህም ደግሞ ከዘላለማዊነቱ ጋር የሚፃረር ይሆናል:: በትርጓሜም ፍጥረት ፈጣሪ የሚያስፈልገው ማለት ነው:: ፍጥረቶች እንዲኖሩ ፈጣሪ ወደ ህልውና ያመጣቸው ዘንድ ያስፈልጋል:: አምላክም ፈጣሪ የማያስፈልገው ነው ምክንያቱም ፈጣሪ ነው:: ይህም ግልጽ የሆነ የሚጻረሩ ሀሳቦች እንደሆኑ ያመላክታል:: ፈጣሪ ፍጥረቱን ሆነ የሚለው አስረጅም ፈጣሪ እንደሚያስፈልገው ያመለክታል፣ ይህም የማላገጥ ሀሳብ ነው:: አምላክ የማይፈጠር፣ ፈጣሪ የማይፈልግና ፈጣሪ የሆነ ከሚለው መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳብ ያፈነገጠ ነው:: ለእርሱም ምላሽ እንደሌለኝ ስላወቅሁኝ “ስለ ምላሹ ላስብበት::” አልኩት::

በዛ ምሽት፣ ልጄ ስለተናገረው ነገር ለረዥም ጊዜ በትኩረት አሰብኩበት:: እየሱስ የፈጣሪ ልጅ የሚለው ሀሳብም ለኔ ከእንግዲህ ወዲያ ትርጉም የማይሰጥ ሆነ:: እየሱስና አምላክ አንድ እና እኩል ናቸው የሚለውንም ልቀበለው አልቻልኩም:: ወደ ምኝታየ ከመሄዴ በፊትም፣ ልጄም ወደ አምላክ ብቻ እንድጸልይና ወደ ትክክለኛው መንገድ ይመራኝ ዘንድ እንድጠይቅ ነገረኝ:: እኔም ለልጄ ወደ አምላክ መልስ ይሰጠኝ ዘንድ በአንክሮ እንደምጸልይ ቃል ገባሁለት:: ወደ ክፍሌ በመሄድም ልጄ የሰጠኝን መጽሀፍ አነበብኩ:: በመቀጠል፣ ቅዱስ ቁርዐንን በመግለጥ ማንበብ ጀመርኩ:: ልክ ከልቤ ላይ የሆነ ነገር እንደተነሳልኝ ነበር:: የተለየ ስሜት ነበር:: እውነትን በእስልምና አየሁ:: ለምን ነበር ያን ያህል የታገልኩት?

በዛ ምሽት ለአምላክ ብቻ ጸሎት አደረኩ _ ለእየሱስም አይደለም፣ ለማርያምም አይደለም፣ ለመላዕክትም ወይም ለቅዱሳን አይደለም ወይም ለመንፈስ ቅዱስ አይደለም:: ለአምላክ ብቻ እያለቀስኩ ይመራኝ ዘንድ ጠየቅሁ:: እስልምና ትክክለኛ ምርጫ ከሆነ ልቦናየን እና አዕምሮየን ይለውጥልኝ ዘንድ ጸለይኩ:: ወደ ምኝታየም ሄድኩ በቀጣዩ ጠዋት በመንቃት ወደ ልጄ ዘንድ በመሄድ እስልምናን ለመቀበል ዝግጁ እንደሆንኩ አበሰርኩት:: እሱም እጅግ ሀሴትን አደረገ:: ሁለታችንም ማልቀስ ጀመርን:: ሴቷ ልጄና የልጅ ልጆቼ ተጠርተው ሻህዳን ስተገብር ተመለከቱ:: ሻህዳ (የሙስሊም በአላህ አንድ ብቻ መሆን እና መሀመድን(ሰላም እና የአላህ ባረኮት በእርሱ በአላህ መልዕክተኛ ይሁንና)እንደ አምላክ ነብይ መቀበል ነው)::

أشهد أن لا إله إلاَّ الله و أشهد أن محمد رسول الله
በአረብኛ፣ በጣልያንኛ እና በእንግሊዘኛ::
“አሻ-ሃዱ አንላ ኢላሃ ኢላ_አላህ ዋ አሻ_ሃዱ አና መሀመዱን ራሱል_አላህ”
“ከአላህ በስቀር አምላክ የለም እና መሀመድ የእርሱ መልዕክተኛ እና የመጨረሻ ነብይ ነው”

የሻህዳ ቪዲዮ ያድምጡ

 

ሻህዳ የሙስሊም በአላህ አንድነት እና መሀመድን (ሰላም እና የአላህ ባረኮት በእርሱ በአላህ መልዕክተኛ ይሁንና) የአምላክ ነብይ እንደሆነ የመቀበል ማረጋገጫ ነው:: የተለወጠች ሴት እንደሆንኩ ይሰማኛል:: የጨለማ ምንጣፍ ከልቤ እንደተነሳልኝ ሁሉ ደስተኛ ነበርኩ:: የሚያውቁኝ ሁሉ እኔ እንደተቀየርኩኝ ማመን አልቻሉም ነበር:: አንዳንድ ጊዜ እኔ ራሴ ማመን አልችልም! ግን እስላም በጣም ትክክለኛው፣ በጣም ሰላማዊ እና በጣም ግልጽ_ያለ እንደሆነ ይሰማኛል::

ልጄ ወደ ስቴትስ ከተመለሰ በኋላም፣ ሱራህ_አል_ፋቲሃን እንዴት ማለት እንደምችል ተማርኩኝ እንዲሁም ጸሎቶችን እንዴት መተግበር እንዳለብኝ እየተማርኩ ነው:: አሁን ሙስሊም ከመሆኔ በስተቀር፣ ህይወትንም እንደቀድሞው እየመራኋት ነው:: የቤተሰብ ግንኙነቶች ላይ ከልጄ ጋር መሳተፍ እወዳለሁ እንዲሁም ደግሞ ማህበረሰባዊ ክስተቶች ላይም እሳተፋለሁ:: የቤተሰብ እና የጓደኛ ሰርግ ላይ፣ ሄና ፓርቲ ላይ፣ አቂቃህ(የህጻናት እጥበት) እንዲሁም ደግሞ አንድ ሰው ሲሞት በሚደረጉ መሰባሰቦች ላይ እሳተፋለሁ:: ወደ እስልምና ከተቀየርኩ ከ 6 ወራት በኋላ፣ በአንድ ልብ በሚነካ እና እስልምና ምን ያህል የተዋበ ሀይማኖት እንደሆነ በሚያሳይ የቀብር ስነ ስርዐት ላይ ነበርኩ:: አንድ ልጅ በህመም ምክንያት ህይወቱ ያልፋል:: ልጄም ሀዘንተኞችን ለማጽናናት ለመሄድ በምትዘጋጅበት ጊዜ፣ ቤተሰቦችን ታውቃቸው እንደሆነ ጠየቅኋት:: እርሷም እንደማታውቃቸው ነገረችኝ:: እኔም እንደዛ ከሆነ ለምን እንደምትሄድ ጠየቅኋት:: እርሷም “ቤተሰቦች በሀዘን ላይ ስለሆኑ፣ በእስልምና የምችለውን ያህል ድጋፍ አደርግላቸው ዘንድ ግዴታ አለብኝ” አለችኝ:: እኔም ለባብሼ አብሬያት ለመሄድ ወሰንኩ:: ከልጄ ጋር በመሆን የልጁን ቤተሰቦች ለማጽናናት በሄድኩበት ጊዜ እዚያ የተገኘውን ሀዘንተኛ ሰው ብዛት በማየት በጣም ተደመምኩ:: ይህን ያህል ሰው ቤተሰቡን ለመደገፍ መምጣቱ ልቤን የነካና ያስገረመኝ ነበር:: ቤተሰቡ ሀዘን በተቀመጠበት ሰዐት ማሰብ የምችለው ነገር ቢኖር ያ ሁሉ ሰው ድጋፋቸውን የመስጠት ኋላፊነት ተሰምቷቸው መገኘታቸው እስላም ምን ያህል የተዋበ ሀይማኖት እንደሆነ ነው:: ያ አንድ ክስተትም፣ ሙስሊሞች በሌላው ሀዘን ጊዜ የሚያሳዩት ማጽናናት የእስልምናን ውበት የሚያረጋግጥ ነው::

አሁን ሙስሊም ከሆንኩ ስምንት አመቴ ነው፣ አላሀምዱሊላህ:: ከዛ ጊዜ ጀምሮ፣ ከወንድ ልጄ ጋር እና ከሴት ልጄ ጋር በመሆን ሁለት ጊዜ ዑምራህ ተግብሬያለሁ:: ወንዱ ልጄ፣ ሴቷ ልጄ እና እኔ ሆነን ቃባህ(መካ ከተማ ውስጥ፣ ሳዑዲ አረቢያ) እና የቅዱስ ነብዩን መስጊድ ጎብኝተናል:: 75ኛ የልደት በዐሌንም አከበርኩኝ አላሀምዱሊላህ:: አንዳንድ ጊዜ በልጄ ጋር ያደረስኩበት አስቸጋሪ እና አሳዛኝ ጊዜያቶችን አስባለሁ፣ ግን ልጄ እኔን ለማገልገል እና እኔን ወደ እስልምና ለማምጣት ምክንያት ስለሆነ በጣም ደስተኛ ነው:: በመቀጠልም እንዲህ አለ፣ ነብዩ (ሰዐወ) ለሰው ልጅ እንደተናገረው “ገነት በእናቶች እግር ስር ትገኛለች” ይላል:: የሀዲስ ትርጓሜውም እናትህን ልትንከባከባት እና ልታገለግላት ይገባል ነው:: በእኔ እግር ላይ በመሆን በእርግጥም ለእኛ ገነትን እናገኛለን:: ሴቷ ልጄ የተወሰነ ጫና ብታሳድርብኝ ኑሮ፣ ምናልባትም ከዛን ጊዜ ቀድሞ ሙስሊም እሆን ነበር:: ግን ልጄ እንዳስታወሰኝ የአላህ እቅድ የሁሉም ምርጡ ነው:: እናም እርሱ ብቻ ነው ለሰው ልጅ ሂዳያ(መምሪያ) መስጠት የሚቻለው::

“አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው”

(ቅዱስ ቁርዐን 28:56)

አላህ በልዩ ሁኔታ ያከበረኝ ወደ እስልምና በመምራት እና እኔን ሙስሊም በማድረግ ነው፣ እናም ኢንሻ አላህ ከልጄ ጋር ገነት መግባት::
« አሜን »