የሀጅ እና ኡምራ መመሪያ

አውርድ / አትም።

የሀጅ እና ኡምራ መመሪያ

የሀጅ እና ኡምራ መመሪያ መጽሐፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ቅርጸት። 11 ሜባ


አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ

አልሀምዱ ሊላህ ወደ መካ ለሚደረገው የሀጅ እና ኡምራ ጉዞ መመሪያ የሚሆን እጥር ምጥን ያለ
ፁሁፍ ከተለያዩ ኪታቦች በማውጣጣት ለማዘጋጀት በቅተናል፡፡ይዘቱን እና ትክክለኛነቱን
ለማረጋገጥ በሳኡዲ አረቢያ እና በመላው አለም በሚገኙ አሊሞች በተደጋጋሚ ተገምግýል፡፡
እያንዳንዱ ሂደት የተለያዩ ኪታቦችን ማገላበጥ ሣያስፈልግ በግልፅ ተብራርቷል፡፡በዚህም ምክንያት
ይህ መመሪያ ይዞ ለመንቀሳቀስ እንዲያመች ከአንድ ገፅ እንዳይበልጥ እንደዚሁም ቀላል እና
ተጣጣፊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህ አንድ ገፅ ሀጅዎትን ቀላል እና ተቀባይነት ያለው ያደርጋል ኢንሻ
አላህ፡፡ ፅሁፉ በሶስት መልክ ይገኛል፡፡

1. ደብዳቤ (ቁመት 279.4ሚሊ ሜትር፤ ስፋት215.9ሚሊ ሜትር)
2. ኤፎር ወረቀት መጠን (ቁመት 297ሚሊ ሜትር፤ ስፋት210ሚሊ ሜትር)
3. እና በደንብ ለማየት እንዲያስችል በትልቁ የተፃፈ የህግ ወረቀት መጠን (ቁመት 355.6ሚሊ
ሜትር ስፋት 215.9ሚሊ ሜትር)

እርስዎን ለመርዳት ይህ የሀጅ እና ኡምራ መመሪያ የሚከተለውን ያቀርባል

  • የእያንዳንዱን ስነስርአት አፈጻጸም ደረጃ በደረጃ ያብራራል
  • ሰፋ እና መርዋህ የሚገኙበትን ቦታ ለማወቅ እንዲረዳዎት የካእባን ካርታ
  • በምስል የተደገፈ የጠዋፍ አደራረግ
  • የሚደረጉ ዱአዎችን አይነት፤ቦታ እና ጊዜ
  • የአስፈላጊዎቹን ጉዞዎች ኪሎ ሜትር እና ማይል
  • ተጠቃሚውን መረጃዎችን በፍጥነት እንዲያመሳክር የሚያስችሉት የድረ ገፅ ምልክቶች

ይህ ልዩ የሀጅ መመሪያ የተለያዩ nንn ተናጋሪዎችን ያገለግላል፡፡በሚከተሉት ቋንቋዎች በወርድ
ወይም ፒዴ ኤፍ መልክ የተዘጋጀውን መመሪያ በነፃ ዳውንሎድ ማድረግ ይችላሉ፡፡

አማርኛ፣አልባኒያንኛ፣አረብኛ፣ቻይንኛ፣ሆላንድኛ፣እንግሊዘኛ፣ኢራንኛ፣ፈረንሣይኛ፣ጀርመንኛ፣
በሶስት የሕንድ ቋንቋዎች(ጉጀራት፣ቴሉጉ፣ሂንዲ)፣ኢንዶኒዥያንኛ፣ጣሊያንኛ፣ጃፓንኛ፣ማሌይኛ፣
ፖርቹጋልኛ፣ራሺያኛ፣ሲሪላንኪኛ፣ስፔንኛ፣ታጋሎግኛ፣ታሚልኛ፣ቱርክኛ እና ኢንሻአላህ በቅርቡ
በሌሎችም nንnዎች ይጀምራል፡፡መመሪያ ፅሁፉ ላይ የሚገኙ የአረብኛ nንn ቃላትም በእነዚህ
nንnዎች ፊደላት ተፅፈዋል