Page 8
The Islamic Bulletin
Purpose Of Life In Amharic
እስላም የዘላለም አምላክ፣ ያለምንም ቤተሰብ፣ ብቸኛ
አምላክ እንደሆነ የሚመሰክር ነው:: እስላም ለነብያት ራዕይ
ይገልጹ ዘንድ የተላኩ መላዕክትን ህልዉና የሚያረጋግጥ
ነው:: ለነብያት መልዕክትን የሚሸከሙ:: ነፋሳትን፣ ተራሮችን፣
ውቅያኖሶችን፣ የሚቆጣጠሩና አምላክ እንዲሞት ያዘዘውን
ነብስ የሚወስዱ ናቸው:: እስላም ሁሉም የዘላለም አምላክ
መልዕክተኞች እና ነብያት ትክክለኛ ሰወች እንደሆኑ የሚያረጋግጥ
ነው:: የተላኩት ሁሉም በዘላለም አምላክ አማካኝነት ለፍጥረታት
ሁሉ የመጨረሻዋን ቀን ለማረጋገጥ የመጡ ናቸው:: እስላም
ክፉንና መልካሙን የሚያረጋግጥ የዘላለም አምላክ እንደሆነ
ያረጋግጣል:: በመጨረሻም፣ እስላም ከሞት በኋላ ትንሳኤ እንዳለ
ያረጋገጠ ነው::
እስላም እንደ ትልቅ ቤት ነው:: እናም ሁሉም ቤት
በመሰረት እና በምሰሶ ተደግፎ መሰራት አለበት:: ምሰሶ እና
መሰረት:: ቤትንም ስትገነቡ በህግ ነው:: ምሰሶዎቹ ህጎች ናቸው!
እና ቤታችሁን ስትገነቡ፣ ህጎችን መከተል አለባችሁ::
የእያንዳንዱ ሙስሊም መሰረታዊ ግዴታወቹም ቀላል
እና በ 5 የሚጠቃለሉ ናቸው፣ እነዚህ አምስት ምሰሶ የሚባሉትም:
እምነት፣ አምልኮ፣ ጾም፣ መዘከር እና ሀጂ ማድረግ ናቸው::
በእስላም ይበልጥ ጠቃሚው ህግ የፈጣሪ አንድ
ብቸኝነትን ማስቀደም ነው:: ይህም ማለት፣ ቤተሰብ የለለው
አምላክ ብቻ:: ከአምላክ ጋር ሌላ ምንም ነገር አለማምለክ::
ምእመናን አምላክን ያለ ምንም የቄስ ወይም የቅዱሳን አማላጅነት
በቀጥታ የሚያመልኩበት:: አምላክን ማለት የሌለባችሁን ነገር
ማለት እንደሌለባችሁ:: “አባት፣ ወንድ ልጅ፣ ሴት ልጅ፣ እናት፣
አጎት፣ አክስት፣ ታማኝ ሰወች አሉት” አለማለታችሁን:: አምላክን
ማለት የለላባችሁን ነገር ማለት እንደሌለባችሁ:: እራሳችሁን
ምስክር ስታደርጉ፣ በራሳችሁ ትፈርዳላችሁ:: የፈለጋችሁትን ፍርድ
ትወስዳላችሁ:: ወይንም ከሰላምና ከገነት ትፈርዳላችሁ ወይም
ራሳችሁን ለግራ መጋባት፣ ለተስፋ መቁረጥ፣ ለገሀነመ እሳት እና ለ
ቅጣት ትፈርዳላችሁ:: በራሳችሁ ትፈርዳላችሁ::
ስለዚህ ራሳችሁን ጠይቁ፣ “አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ
ምስክር መሆን አለብኝ?” ይህን ጥያቄ ራሳችሁን ስትጠይቁ፣
መልሳችሁ፣ “አወ፣ ምስክር ነኝ” የሚል ይሆናል:: በመቀጠልም
ይህን ጥያቄ ራሳችሁን ጠይቁ:: መሀመድ የዘላለም አምላክ
መልዕክተኛ እንደሆነ ምስክር መሆን አለብኝ? “አወ፣ ምስክር
እሆናለሁ::” ለዚህ ምስክር ከሆናችሁ ሙስሊም ናችሁ:: እናም
የነበራችሁበትን መለወጥ አይኖርባችሁም:: እንዲሁ ምን
እንደነበራችሁ በአስተሳሰባችሁና በተግባራችሁ መለወጥ
አለባችሁ::
በመጨረሻም፣ ቀጥተኛና ግልጽ ጥያቄ ልጠይቃችሁ::
እየተናገርኩ ያለሁትን ተረድታችሁኛል? በተናገርኩት ነገር
ከተስማማችሁና ወደ እስልምና ለመግባት ከተዘጋጃችሁ፣
ሙስሊም ለመሆን ዝግጁ ናችሁ:: ሙስሊም ለመሆን፣
በመጀመሪያ ሻህዳን “የእምነት ምስክርን” መድገም ይኖርባችኋል፤
እሱም በአምላክ አንድነት ማመን እና መሀመድን የአምላክ
መልዕክተኛ አድርጎ መቀበል ነው::
لا إله إلا الله محمد رسول الله
ላ ኢላህ ኢላ አላህ፣ መሀመድ ረሱሉላህ
ከአምላክ በቀር አምላክ የለም፣ እና መሀመድ የአምላክ
መልዕክተኛ ነው::
አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ ምስክር እሆናለሁ::
መሀመድ የአላህ መልዕክተኛ እንደሆነ ምስክር እሆናለሁ::
የሚከተለውን ቪዲዩ ይመልከቱ::
http://www.islamicbulletin.org/purpose/shahada/sh_amharic.mp4አላህ ይባርከን:: አላህ ይምራን:: ሙስሊም ላልሆናችሁ የዚህ
ጽሁፍ አንባቢያን መናገር የምፈልገው - - ለራሳችሁ በጣም
ታማኝ እንድትሆኑ ነው:: ስለአነበባችሁት ነገር አስቡ:: ይህን
መረጃ ውሰዱና በደንብ አብላሉት:: ከሙስሊም ጋር ቁጭ ብላችሁ
የእስልምናን ውበት ይበልጥ እንዲገልጹላችሁ አድርጉ:: ወደ ቀጣዩ
ደረጃም ተሸጋገሩ!
እስልምናን ለመቀበልና ሙስሊም ለመሆን ስትዘጋጁ፣ በይፋ
ሙስሊም ከመሆናችሁ በፊት ታጠቡ:: እስልምናን ተቀበሉ:: ስለ
እስላም እወቁ:: እስልምናን ተግብሩ:: እናም አላህ ካቀረበላችሁ
ሽልማት በደስታ ተቋደሱ፣ ምክንያቱም እምነት እንደውለታ
የምትወስዱት አይደለም:: በተግባር ካላዋላችሁት፣ ጣዕሙን
ታጣላችሁ:: አላህ ይምራን:: አላህ ይርዳን:: እናም በዚህ አጋጣሚ
ይህን ንግግር ላደርግ በመቻሌ ክብር ይሰማኛል::
ُ
ه
ُ
ات
َ
ك
َ
ر
َ
بـ
َ
و
ِ
الله
ُ
ة
َ
م
ْ
ح
َ
ر
َ
و
ْ
م
ُ
ك
ْ
ي
َ
ل
َ
ع
ُ
م
َ
لا
َّ
الس
አሰላሙ አሊኩም ወ ረመቱላሂ ወ በረካቱ
“ሰላም በአንተ ላይ ይሁን እንዲሁም የአላህ ምህረትና ባረኮት”
ሙስሊም ለመሆን ከፈለጋችሁና በእስልምና ላይ ተጨማሪ መረጃ
ከፈለጋችሁ፣
እባካችሁ በ
info@islamicbulletin.orgላይ ኢሜይል ያድርጉልን
ወይም ይህንን ገጽ ይጎብኙ
www.islamicbulletin.org http://www.islamicbulletin.org/services/foreign.htm#a2a http://www.islamicbulletin.org/services/new_muslims/carla_amharic.html http://www.islamicbulletin.org/purpose/amharic/flipping/index.html http://www.islamicbulletin.org/purpose/amharic/purpose.html